የድረገፅ መረጃ

ይህ ተዋህዶ መልሶች የተሰኘው ገፆችን ነው የዚህ ገፅ አላማ ምዕመናን ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ጥያቄዎች መመለስና በአማናዊት እምነታቸው ማፅናት ነው ::

ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሠረታት ቀን አንስቶ ይህች ቅድስት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ አልፋለች :: ዛሬም በኛ ዘመን በፈተና ውስጥ ናት ከነዚህ ፈተናዎች መካካል የትውልዱ እውቀት ማጣት ዋነኛው ነው፡ ፡ ይህንንም ክፍተት በመጠቀም የበግ ለምድ የለበሱ እምነትን የሚሸራርፉ አሳቾች ግፋ ሲልም ሃይማኖትን ሙሉ በሙሉ የሚያስጥሉ ከሃዲያን ልጆቿን ለመብላት ያንዣብባሉ የተበሉም ብዙዎች አሉ :: ይህ ሃይማኖትን መተው ወይንም መቀየር ብተኛው ፈተና አይደለም :: ብዙዎች ዛሬ በቤተክርስቲያን ቅጥር በአካል ተገኝተው እየዋሉ እያደሩ በመንፈስ ግን ሙታን የሆኑ የሚደረገውን አብሮ ከማድረግ ባለፈ እውቀቱ የሌላቸው እልፍ ናቸው ::

ጌታ ቢፈቅድና ቢረዳን ይህንን ችግር በጥቂቱም ቢሆን ለመፍታት ይህንን ድረ ገፅ ምዕመናን ያላቸውን ጥያቄ የሚያቀርቡበትና ምላሽ የሚያገኙበት እንዲሆን አስበን አዘገጅተናል ::

በዚህ ገፅ የሚቀርቡት አስተምህሮቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ክርስትናን መሠረት ያደረጉ ናቸው :: እውቀቱ ያላችሁ ምዕመናን እና የቤተ ክርስቲያን ሊቀውንት በማንኛውም አገጣሚ ከዚህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለተሰማማ ፅሁፍ ካስተዋላችሁ ይፃፉልን የተገኘውን ስህተት መርምረን ለማረም ዝግጁ ነን ::

Get in touch

Copyright © 2024 Tewahedo Answers. All rights reserved.